አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተውጣጡ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና የሐይማኖት አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤም ለጎብኚዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በአንድነት ዘምተው ድል ያደረጉበት የዓድዋ ድል በልኩ ቋሚ መታሰቢያ እንዲኖረው መደረጉ እንዳስደሰታቸውም ጎብኚዎቹ መናገራቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
የዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚያኮራ እና ለትውልድ የሚተላለፍ ቋሚ ቅርስ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡