አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኦስትሪያ ማዕድን ፍለጋን ጨምሮ ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር ) በኢትዮጵያ የኦስትሪያ አምባሳደር ሲሞን ኬናፕ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት በማዕድን ፍለጋና ልማት፣ በአቅም ግንባታና ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡
ሃብታሙ (ኢ/ር) በዘርፉ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለአምባሳደሯ ማብራራታቸውን የማዕድን ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
አምባሳደሯ በበኩላቸው የሀገራቸው የማዕድን ኩባንያዎች እና መንግሥታቸው ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡