Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ዮርዳኖስ በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከዮርዳኖስ ቱሪዝም ሚኒስትር መክራም ሙስጠፋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ናሲሴ÷ኢትዮጵያና ዮርዳኖስ በታሪክ፣ በባሕልና ሃይማኖት የተሳሰሩ ሀገራት መሆናቸውን አአውስተዋል፡፡

ሀገራቱ የጋራ የቱሪዝም ጥቅሎችን በማዘጋጀት በትብብር ለመስራት መስማማታቸውንም ገልጸዋል።

መክራም ሙስጠፋ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የታሪክ፣ ባህል፣ ተፈጥሮ እና የውበት መገኛ ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያና ዮርዳኖስ በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ለሀገራቱ ሕዝቦች ትልቅ ሚና እንዳለው ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያ ቅርሶቿንና ባህላዊ ክዋኔዎቿን በዩኔስኮ በማስመዝገብልምድያላት ሀገር መሆኗን ጠቁመው÷በዚህ ረገድ ዮርዳኖስ በርካታ ተሞክሮ ትወስዳለች ብለዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በዘርፉ የሰው ሃይል ማብቃት የሚያስችሉ ሥራዎችን በጋራ ለመስራት መስማማታቸውም ተመላክቷል፡፡

በዘመን በየነ

Exit mobile version