አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ውስጥ ለዩክሬን ጦር ሃይል የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ የተጠረጠረች የአሜሪካና ሩሲያ ጥምር ዜግነት ያላት ግለሰብ በፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏን የሩሲያ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
ኤጀንሲው እንዳስታወቀው÷ ስሟ ያልተገለፀ የ33 ዓመቷ የሎስ አንጀለስ ተወላጅ በድብቅ የዩክሬንን ጦር ለመርዳት ገንዘብ ስታሰባስብ በይካትሪንበርግ ከተማ በሩሲያ ፌደራል የፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡
ግለሰቧ ከፈረንጆቹ 2022 የካቲት ወር ጀምሮ የዩክሬን ከሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመመሳጠር ገንዘብ ሰብስባ ለዩክሬን ጦር መድሃኒት፣ የጦር መሳሪያና ተተኳሽ መግዛቷ ተገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዋ ከዚህ ቀደም በዋሽንገተን የኬቭን አገዛዝ ለመደገፍ በተደረጉ ህዝባዊ ሰልፎች ላይ መሳተፏም ተመላክቷል፡፡
ግለሰቧ በሩሰያ ፍርድ ቤት በከፍተኛ የሀገር ክህደት ወንጀል ክስ እንደሚመሰረትባት የተገለፀ ሲሆን ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች በሩስያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 275 መሰረት ከ12 እስከ 20 ዓመት የሚደርስ እስር እንደሚጠብቃት መገለጹን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡
#Russia #Ukrain
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!