አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት የ49 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና የባንኩ ፕሬዚዳንት ሲዲ ኦልድ ታህ (ዶ/ር) ተፈራርመውታል፡፡
ድጋፉ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ምርታማነትን ለማጎልበት የሚውል መሆኑ ተመላክቷል።
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚደገፈው ይህ ፕሮጀክት በአራት የተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!