የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው

By Amele Demsew

February 19, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

ውይይቱ የክልሉ ሕዝብ የሚያነሳውን የመልካም አሥተዳደር፣ የልማት ሥራዎች እና ሌሎች ጥያቄዎችን መመለስ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በውይይት መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ሃላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የክልሉ ም/ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡