Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳ ስልጣን ርክክብ ለማካሄድ የተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ሳምንት በመጪው ረቡዕ ለሚካሄደው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳ ስልጣን ርክክብ በሜኤ ቦኮ የተለያዩ ስነስርዓቶች እየተከናወኑ ነው፡፡

ከገዳ ሀርሙፋ ወደ ገዳ ሮበሌ ለሚደረገው ሽግግር ነው አባ ገዳዎች በአርዳ ጂላ ሜኤ ቦኮ ከትመው ስነ ስርዓቶችን  እያከናወኑ የሚገኙት፡፡

የምዕራብ ጉጂ ዞን ኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ ገመቹ ገብረ ማርያም÷ በስነ ስርዓቱ የገዳ ስርዓት ለሰው ልጅ፣ ለእንስሳት እና ለተፈጥሮ የተሰጠው መብት አፅንኦት የሚያገኝበት የተለያዩ አዋጆች እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችም ስርዓቱ የሰጣቸውን መብትና ግዴታ በመተንተን ትውልድ እንዲያስቀጥለው እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የስልጣን ርክክብ አባ ገዳ ጂሎ ማንዶ ስልጣን በማስረከብ በሀዩ ገዳነት ያገለግላሉ ተብሏል፡፡

በማርታ ጌታቸው

 

 

Exit mobile version