አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በርካታ አንድሮይድ መተግበሪያ የሚጠቀሙ ስልኮች ለብልሽት እየዳረገ ያለው ፎቶ አነጋጋሪ ሆኗል።
በርካታ የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች ይህን የሐይቅ፣ ጉም ውሰጥ የምትታይ የጠዋት ፀሐይ እና የዛፍ ቅርንጫፎች የሚያሳይ ፎቶ በስልካቸው የፊት ገፅ ካደረጉ በኋላ ስልካቸውን ከተለመደው ውጭ እያደረገ እንደሆነ እየተነገረ ነው።
የአንድሮይድ ስልክ ያላቸው ሰዎቸ ይህን ፎቶ በማንኛውም መልኩ በስልካቸው በመጫን የፊት ገጽ ካደረጉ ስልካቸው ላይ የነበሩ ፋይሎችን በማጥፋት እና ሌሎች ያልተለመዱ ባህርያት እንዲያሳዩ ምክንያት ይሆናል ነው የተባለው፡፡
ይህን ተከትሎም ሳምሰንግ በግሪጎርያውያኑ ሰኔ 11 ጥገና አደርጋለሁ ሲል ቀጠሮውን ከደንበኞቹ ጋር አድርጓል።
አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም 11ኛው አዲስና ዘመናዊ ምርት በዚህ ሳምንት ሊለቅ እንደነበር ዘገባው ያስታወሰ ሲሆን፥ ሆኖም በዚህ ፎቶ ምክንያት 11ኛ ምርቱን መዘግየቱ ግድ ሆኗል ነው የተባለው።
ይህ ፎቶ የአንድሮይድ ስልኮችን ለይቶ እንዲያጠቃ ተደርጎ የተሰራበት ምክንያት ግን ለይተው ማወቅ አለማወቃቸው ላይ የተባለ ነገር የለም፡፡
ነገር ግን ኬን ሙንሮ እና ዴቭ ሎጅ የተባሉት የቴክኖሎጂ ባለሙያወች የፎቶው ቀለማት ከስልኮቹ ቀለማት ጋር መመጣጠን አለመቻል ያስከተለው ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ