Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቴሌኮሙኒኬሸን፣ ቱሪዝምና ቆዳ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር መሥራት እፈልጋለሁ- ዛምቢያ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛምቢያ በቴሌኮሙኒኬሸን፣ ቱሪዝምና በቆዳ ኢንዱስትሪ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መሥራት እንደሚፈልግ የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ እና ሳይንስ ሚኒስትር ፍሌሲ ሙታቲ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ በቴሌኮሙኒኬሸን መሰረተ ልማት ከዛምቢያ በላቀ ደረጃ ላይ ስለምትገኝ በዘርፉ ልምድ እና ዕውቀት ለመሸመት ጽኑ ፍላጎት አለን ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል ሚኒስትሩ፡፡

በተጨማሪም ሁለቱም ሀገራት ዕምቅ የቱሪዝም አቅም እንዳላቸው ገልጸው÷ በዘርፉ ልምድና ዕውቅት በመለዋወጥ በትብብር መሥራት እንደሚያስችላችው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም ኢትዮጵያ በቆዳ ውጤቶች ስኬታማ ተግባራትን እያከናወነች መሆኗን ያመላከተቱት ሚኒስትሩ÷ ዛምቢያ በዚህ ረገድ በጋራ መሥራት ትፈልጋለች ብለዋል፡፡

Exit mobile version