የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ

By Amele Demsew

February 18, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያስተዋውቅ መድረክ በስዊድን ተካሂዷል፡፡

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ምሕረተአብ ሙሉጌታ÷ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለኢኮኖሚ ልማት ሂደቶችና እየተገኙ ስላሉ ውጤቶች በመድረኩ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር ስለምትጫወተው ግንባር ቀደም ሚና ማስረዳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ መዕዋለ ንዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሃብቶች ስለሚሰጡ ማበረታቻዎች፣ የገበያ ትስስሮች፣ አመቺ ፖሊሲዎችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎችም አብራርተዋል፡፡

የስዊድን ባለሃብቶችም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የስዊድን አፍሪካ ንግድ ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የስዊድን ባለሃብቶች ተገኝተዋል፡፡