Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፈረንሳይ እና ዩክሬን ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ እና ዩክሬን በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ በፈረንሳይ ፓሪስ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ÷ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ እና ፕሬዚዳንት ማክሮን በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

በተጨማሪም ፈረንሳይ ለዩክሬን ተጨማሪ የ3 ነጥብ 23 ቢሊየን ዩሮ ጦር መሳሪያ እርዳታ እንደምታደርግም ቃል ገብተዋል ፕሬዚዳንት ማክሮን፡፡

ድጋፉ ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ያለመ እንደሆነ መገለጹን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ዩክሬን በቅርቡ ከጀርመን እና ብሪታንያ ጋር ተመሳሳይ የወታደራዊ ስምምነት መፈራረሟ የሚታወስ ነው፡፡

Exit mobile version