Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸው ተገለጸ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በኤፍኤስአር ተሽከርካሪ የተለያየ አይነት 1 ሺህ 190 የሞባል ቀፎዎች እና 4 ሺህ 996 የሞባይል ባትሪዎች ናቸው ተብሏል፡፡

መነሻውን ከምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በማድረግ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን በመኪናው ቦዲ ውስጥ ደብቆ ወደ አዳማ ከተማ በመግባት ላይ እያለ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በአዳማ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ የተያዙት የአካባቢው ህብረተሰብ ባደረገው ጥቆማ መሰረት መሆኑን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃው 20 ሚሊዮን 81 ሺህ ብር ግምት ያለው ሲሆን በኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን አዳማ ቅርጫፍ ገቢ ተደርጎ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

ከዚህም ባሻገር በአዳማ ከተማ ከኢትዮ-ቴሌኮም እውቅና ውጭ 721 ሲም ካርዶችን ተጠቅሞ የቴሌ ማጭበርበር ሲፈጽም የተገኘ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዳማ ፖሊስ ጨምሮ አመልክቷል።

Exit mobile version