Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ከ259 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 259 ሚሊየን 35 ሺህ 835 ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ነው።

በጉባኤው ሁለተኛ ቀን ተጨማሪ በጀት ያጸደቀ ሲሆን፤ ተጨማሪ በጀቱ ከክልሉ ማዕከል፣ ከወንዶገነት ከተማ፣ ከአለታ ጩኮ ከተማና ከአለታ ጩኮ ወረዳ አስተዳደሮች እንደሚሰበሰብ ተጠቁሟል።

ተጨማሪ በጀቱ ለደሞዝ፣ መደበኛና የካፒታል ስራዎችን ለማከናወን እንደሚዉል ተገልጿል።

በታመነ አረጋና ጥላሁን ይልማ

Exit mobile version