የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀስሥላሴ ከዚምባብዌ አቻቸው ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

February 15, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስሥላሴ ከዚምባብዌ አቻቸው አምባሳደር ፌድሪክ ኤም ሻቫ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ።

ሚኒስትሮቹ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ትብብር ላይ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

በውይይታቸውም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የባለብዙ ወገን አጋርነትን ለማጠናከር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

#Ethiopia #Zimbabwe

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!