Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና አንጎላ ሁለት ስምምነቶችን ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና አንጎላ በዛሬው ዕለት ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ እና የአንጎላ አቻቸው ቴቴ አንቶኒዮ ተፈራርመዋል፡፡

በዚህም ሚኒስትሮቹ አጠቃላይ የትብብር ስምምነት እና የፖለቲካ ምክክር ማድረጊያ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ኀብረት 44ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተፈረመው፡፡

Exit mobile version