Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሚቺጋኑ ግለሰብ የ70 ዓመት የፍቅር ደብዳቤው እንቆቅልሽ ለመፍታት እየሞከረ መሆኑ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ የሚቺጋን ሰው በጨረታ ከገዛው እርሻ የመሳሪያ ሳጥን ውስጥ ያገኘውን የ70 አመት የፍቅር ደብዳቤ እንቆቅልሽ ለመፍታት እየጣረ መሆኑ ተሰማ።

ዓለም የስልክና የዘመናዊ መገናኛ ውጣ ውረድን የማቅለል እድል ሳታይ በፊት ደብዳቤ ናፍቆትን መወጫ፣ ፍቅርን መግለጫ፣ ቅራኔን መፍቻ በመሆን አገልግሏል፡፡

በተለይም የፍቅር አጋሩን የናፈቀ ወታደር ደብዳቤ ልብ ጠጋኙ፤ ተስፋ ሰናቂ ነገውን መመልከቻ መሳሪያው ነበር፡፡

በዚህም ታሪክ የተፈጠረው ይሄው ነው፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሪክ ትሮጃኖቭስኪ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2017 እርሻን በጨረታ ይገዛል፤ ከዓመታት በኋላም በገዛው እርሻ አንድ አሮጌ ደብዳቤ በመሳቢያ ውስጥ ያገኛል፡፡

ደብዳቤውን ከፍቶ ሲያነበው የተፃፈው ከ70 ዓመታት በፊት በጦር ኃይሎች ኮርፖራል ኢርቪን ጂ ፍሌሚንግ በተባለ ግለሰብ የተጻፈ ነው፡፡

ይህ ደብዳቤ ከሳን ፍራንሲስኮ ወደ ግራንድ ራፒድስ ሜሪ ሊ ክሪብስ ወደምትባል የልቡ ሰው የተላከ ነው፡፡

በደብዳቤው ፍሌሚንግ ከፍቅር አጋሩ ክሪብስ ጋር ለተፈጠረ አለመግባባት ይቅርታውን፣ ጊዜ ስለማያደበዝዘው ፍቅሩ እንዲሁም ከተልዕኮው ሲመለስ ስለሚቀልሱት ጎጆ ተከትቧል፡፡

“ይህ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ነው፤ በአሁን ጊዜ ሰዎች የፍቅር ደብዳቤ አይጽፉም፤ ወታደሩ ለፍቅር አጋሩ የሰነደላትም ተራ ቃላት ሣይሆኑ ግጥምን ይመስላል” ሲልም ነው የሚቺጋኑ ግለሰብ የሚናገረው፡፡

ትሮጃኖቭስኪ ደብዳቤውን የጥንዶቹን ዘመዶች በማግኘት ለመስጠት እየሞከርኩ ነው ሲልም መናገሩን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡

#Letters #OddNews

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version