የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የዓለም መንግሥታት ጉባኤ እየተሳተፉ ነው

By Amele Demsew

February 13, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ከንቲባዋ በቆይታቸው በከተማ ፕላንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደር ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረጉ የጎንዮሽ ውይይቶች ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡:

በመድረኩ ላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) እንዲሁም የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ተሳታፊ ሆነዋል::