አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ሴኔት ለእስራኤል፣ ዩክሬን እና ታይዋን የ95 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቋል፡፡
ድጋፉ በሴኔቱ 67 ለ32 በሆነ አብላጫ ድምፅ መፅደቁ የተገለፀ ሲሆን የሴኔቱ የሪፐብሊካን ተወካዮች ውሳኔውን መቃወማቸው ተመላክቷል፡፡
ድጋፉ የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የዩክሬን እና እስራኤል ወታደራዊ ሀይልን ለማጠናከር የሚውል ስልመሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ለታይዋን እና በጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ይውላል ነው የተባለው፡፡
ከድጋፉ በተጨማሪ ለአሜሪካ የደህንነት ስጋት ነው የተባለውን የአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድንበርን በተመለከተ ሴኔቱ ውሳኔ ሳያሳልፍ መቅረቱን ዩኤስኤ ቱዴይ ዘግቧል፡፡