የሀገር ውስጥ ዜና

የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

By Amele Demsew

February 13, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

ከትናንት ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ፣ ቡሩንዲ፣ ኬኘ ቨርዴ፣ ኮሞሮስ እና የካሜሩን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በህብረት 44ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እና በ37ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

እንዲሁም የደቡብ ሱዳን አለም አቀፍ ትብብርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ጀምስ ሞርጋን እና የቱንዝያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናቢ አማር 44ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።