የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቃንና ማረቆ ሕዝቦች የእርቅ ማጽኛ ሥነ-ሥርዓት እየተካሔደ ነው

By Shambel Mihret

February 13, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስቃን እና ማረቆ ወንድማማች ሕዝቦች የእርቅ ማጽኛ ሥነ-ሥርዓት በኢንሴኖ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የመስቃን ቤተ ጉራጌ እና የማረቆ ብሔረሰብ የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

እየተካሄደ ያለው ሥነ-ሥርዓትም የመስቃን እና የማረቆ ወንድማማች (እህትማማች) ሕዝቦች ለዘመናት ያቆዩትን የጋራ እሴት በጽኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ያለመ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡