Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተስተጓጎለው የክረምት ትምህርት በቅርቡ እልባት ያገኛል – ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተስተጓጎለውን የክረምት ትምህርት በቅርቡ እልባት እንደሚሰጠው ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በኮቪድ፣ በ12ኛ ክፍል ፈተናና የአካዳሚክ ካላደሩን ለማጣጣም በሚል የተቋረጠው ትምህርት ቀጣይ እጣፈንታ ምንድነው?” በሚል ጥያቄዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስለጉዳዩ የጠየቃቸው በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ሃላፊ አሰገደች ምሬሳ ችግሩን ለመፍታት ስራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል።

ለዚህም እንዲረዳ በክረምት ደረጃ ለማሻሻል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መምህራን መረጃ እየተጠናከረ እንደሆነ ተናግረዋል።

በክረምት መርሐ ግብር መምህራንን ሲያስተምሩ ከቆዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመጪዎቹ 15 ቀናት ምክክር እንደሚደረግ ወይዘሮ አሰገደች ጠቁመዋል።

ተመራቂዎች ትምህርታቸውን በዚህ ዓመት እንዲያጠናቅቁ ይሰራል ያሉት ኃላፊዋ፤ አጠቃላይ የመረጃ ስራዎች ተጠናቀው የመጨረሻ ውሳኔው በ45 ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግም አንስተዋል።

በክረምት መርሐ ግብር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ መምህራን ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ ይታወቃል።

በአፈወርቅ እያዩ

Exit mobile version