የሀገር ውስጥ ዜና

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ፈተናዎችን በጋራ ማሸነፍ ይጠበቅብናል- አቶ አረጋ ከበደ

By Melaku Gedif

February 10, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ፈተናዎችን በጋራ እና በትብብር ማሸነፍ ይጠበቅብናል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡

በአዳማ ከተማ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት÷ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚከሰቱ ፈተናዎችን በጋራ እና በትብብር ማሸነፍ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን በመፍታት የተጀመረውን ልማትለማስቀጠል በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በየደረጃው የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በጋራ እና በቅንጅት መመከት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው÷ የሥኬቶቻችን መሰረት የሕዝብ ተሳትፎ እና አንድነት ነው ማለታቸውን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወደ ሁሉን አቀፍ ብልጽግና ለመሻገርም የተገኘውን ድል ማጠናከር እና የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ማክሸፍ ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!