የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሞና ሲዳማ ሕዝቦች ላይነጣጠሉ የተጋመዱ ሕዝቦች ናቸው – አቶ ደስታ ሌዳሞ

By Feven Bishaw

February 10, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በመድረኩ የተገኙት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት÷ የኦሮሞ እና ሲዳማ ሕዝቦች ላይነጣጠሉ የተጋመዱና የተሰናሰሉ ሕዝቦች ናቸው ፡፡

ሁለቱ ሕዝቦች በችግር ጊዜ በጋራ የቆሙ፣ ኢትዮጵያን ለማፅናት አብረው የተዋደቁ እና ለጋራ አላማ በጋራ የተሰለፉ ወንድም ህዝቦች ናቸው ሲሉም አውስተዋል፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ ነዋሪዎች የሻሸመኔና የአካባቢው ሕዝብ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን መንግሥት የጀመራቸው የልማት ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

መንግሥት የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ እና የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ መጠቆማቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_televisionበመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!