የሀገር ውስጥ ዜና

ጉምሩክ ኮሚሽን 97 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሰበሰበ

By Amele Demsew

February 10, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉምሩክ ኮሚሽን በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት 97 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እንዳሉት ÷ባለፉት ስድስት ወራት ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች 103 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 97 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡

ገቢው ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከሌሎች ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ነው የተሰበሰበው፡፡

ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም በ9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው መናገራቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡