አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በሁሉም ዞኖች በሚገኙ 20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ፡፡
መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
በውይይት መድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር መክረዋል፡፡
መድረኩ የሕብረተሰቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ተረድቶ ለመፍታት ከማገዙም በላይ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር የሚረዳ መሆኑ ተመልክቷል።