የሀገር ውስጥ ዜና

ለጤና ባለሙያዎች፣ ፖሊስ፣ የትራፊክ ፖሊሶችና የአደጋ መከላከል ሰራተኞች ማስክ ማሰራጨት ሊጀመር ነው

By Tibebu Kebede

June 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዘውዲቱ ሆስፒታል ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና ታካሚዎች የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን አስረክበዋል።

ኢንጂነር ታከለ ለጤና ባለሙያዎቹ የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ያሰባሰባቸውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ የእጅ ጓንት፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል።

ከዛሬ ጀምሮም እንደ ፖሊስ፣ የጤና ባለሙያዎች የትራፊክ ፖሊሶችና የአደጋ መከላከል ሰራተኞች ላሉ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማስክ ማሰራጨት የሚጀምር ይሆናል።

የከተማ አስተዳደሩ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ተቋማት የተለያዩ የጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን እያሰባሰበ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።