አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 30 በርሚል ነዳጅ ከነተሽከርካሪው መያዙ ተገለጸ፡፡
መነሻውን ከሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ዶሎ ባይ ያደረገው ነዳጁ ወደ ሶማሊያ ጁባላንድ ጌደወይኒ ድንበር አልፎ ሊሻገር ሲል በስፍራው ግዳጁን በመወጣት ላይ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት መያዙ ተገልጿል፡፡
ለሀገር የሚገባውን ጥቅም የሚያሳጡ ስግብግብ ነጋዴዎች በየትኛውም የድንበር በር እንደማያመልጡ መገለጹን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡