የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የልማት እና የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ጥያቄዎችን በተመለከተ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

By ዮሐንስ ደርበው

February 06, 2024

👉 በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ባደረኳቸው ምክክሮች የልማት፣ የሕገ-መንግሥት እንዲሁም የወሰን ይገባኛል እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ተነስተዋል፤ ይህን ለመመለሥ በተደራጀ አግባብ አቅደን እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

👉 የባሕርዳር ዓባይ ድልድይ፣ የቅዱስ ላሊበላ ገዳማት ጥገና እና ጎርጎራ በክልሉ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች መልስ መስጠታችን ማሳያዎች ናቸው ብለዋል

👉 የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ጥያቄ በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች እንደሚነሳ ጠቅሰዋል፡፡

👉 በየጊዜው የሚቀደድ ከሚሆን ዘላቂ ሕገ-መንግሥት እንዲኖር እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል።

👉 ከወሰን ይገባኛል ጋር በተያያዘም በአማራ እና በትግራይ በኩል ያሉ የወሰን ጥያቄዎች ዘላቂ ሰላምን እንዲያስገኙ አስበን በስክነት እየሠራን ነው፡፡ ሁለቱ ሕዝቦች የማይነጣጠሉ አብረው የሚኖሩ መሆናቸውንም መገንዘብ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

በዮሐንስ ደርበው