Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ከተመድ ረዳት ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኪሚሽነር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ከተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ራሚዝ አልባካሮቭ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በቅንጅት በጋራ መሥራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ስምሪት፣ በአቅም ግንባታ ሥራዎች እንዲሁም በተለያዩ የፀጥታ ሥራዎች  ላይ በትብብር ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

ራሚዝ አልባካሮቭ ( ዶ/ር)÷ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት በኢትዮጵያ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የፌዴራል ፖሊስ ለሚያደርገው ሙያዊ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት መስራች መሆኗንም አስታውሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.