ስፓርት

ብራይተን ክርስታል ፓላስን አሸነፈ

By ዮሐንስ ደርበው

February 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብራይተን ክርስታል ፓላስን 4 ለ1 አሸንፏል፡፡

ምሽት 12፡00 ሠዓት ላይ በተካሄዱ ጨዋታወች÷ ኒውካስል ከሉተን ታውን 4 አቻ እንዲሁም በርንሌይ ከፉልሀም 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡

የዛሬውን ጨዋታ ውጤት ተከትሎም ብራይተን በ35 ነጥብ 7ኛ፣ ኒውካስል በ33 ነጥብ 9ኛ፣ ፉልሀም በ26 ነጥብ 12ኛ፣ ክርስታል ፓላስ በ24 ነጥብ 14ኛ፣ ሉተን ታውን በ20 ነጥብ 16ኛ እና በርንሌይ በ13 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡