Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ በኢራቅ እና ሶሪያ ሚሊሻዎች ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከቀናት በፊት በዮርዳኖስ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ለተገደሉባት ወታደሮቿ የመጀመሪያውን አፀፋ በኢራቅ እና ሶሪያ በሚገኙ ሚሊሻዎች ላይ ሰነዘረች፡፡
 
የዓየር ድብደባ ጥቃቱ የተሰነዘረው በሰባት ቦታዎች ከ85 በሚልቁ ኢላማዎች ላይ መሆኑን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
 
በጥቃቱም የዕዝና ቁጥጥር ዋና መሥሪያ ቤት፣ የመረጃ ማዕከላት፣ የሮኬቶችና ሚሳኤሎች ማከማቻዎች፣ የሰው አልባ አውሮፕላኖች እንዲሁም የጦር መሣሪያ ማከማቻ ሥፍራዎችን ጨምሮ ከሚሊሻዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ተቋማት ተመትተዋል ተብሏል፡፡
 
የአሜሪ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫም÷ ከቴህራን ጋር ያለውን ግንኙነት የሚቆጣጠር እና የቀጣናውን ሚሊሻዎች የሚያስታጥቀው ክፍልም የጥቃቱ ሰለባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
ኢራን ከዮርዳኖስ ጥቃት ጀርባ እንዳለች አሜሪካ ብትገልፅም÷ ቴህራን በበኩሏ ተሳትፎ የለኝም ስትል ክሱን ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል፡፡
 
ከአሜሪካ በኩል ለሚደርስባት ማንኛውም ስጋት ቴህራን ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷንም ጠቅሷል ዘገባው፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version