የሀገር ውስጥ ዜና

ሆስፒታሉ ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ

By Amele Demsew

February 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በነጻ የሚሰጡት አገልግሎቶችም የሕጻናት ህክምና፣ የውስጥ ደዌ ፣ የጥርስ ፣ የልብ ፣ የቆዳና አባላዘር እንዲሁም የፕላስቲክ ቀዶ – ሕክምና መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ሆስፒታሉ አገልግሎቱን የሚሰጠው “የግብፅ ኮፕቲክ ሚሽነሪ” ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአሜሪካ ሀገር በሚመጡ የሕክምና ባለሙያዎች መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ስለሆነም አገልግሎቱን የሚፈልጉ ታካሚዎች በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 በሆስፒታሉ በመገኘት ሕክምናውን ማግኘት እንደሚችሉ ሆስፒታሉ አስታውቋል፡፡

በትዝታ ደሳለኝ

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!