Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

15ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫል ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ባህሎቻችንን ማወቅ ስብራቶቻችንን መጠገን” በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው 15 ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫል ዛሬ በግዮን ሆቴል ተከፍቷል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ያዘጋጀው ይህ ፌስቲቫል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡

በፌስቲቫሉ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የባህል መንደር ምስረታን ጨምሮ ÷ የአኗኗር ዘይቤ፣ ሐይማኖታዊ ሥርዓቶች፣ የባህላዊ ምግቦችና መጠጦች አዘገጃጀት ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

የማኅበረሰቡን ባህልና በጎ ማኅበራዊ ዕሴቶችን ለማስተዋወቅ፣ የሀገር በቀል ዕውቀትን ለማልማት እንዲሁም የዕደ-ጥበብ ውጤቶችን በማቅረብ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ፌስቲቫሉ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቅሷል፡፡

በፌስቲቫሉ መክፈቻም የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ እንዲሁም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

በመለሰ ምትኩ

Exit mobile version