Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ፓኪስታን የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስተር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከፓኪስታን ገንዘብ ሚኒስትር ሻምሻድ አክታር (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያና ፓኪስታን የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም በፋይናንስ ዘርፉ የሁለትዮሽ ትብብርን ጨምሮ በሀገራቱ የጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነትም ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከፓኪስታን ባንክ ምክትል ገዥ ኢናያት ሁሴን (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸውን በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል በባንኩ ዘርፍ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

Exit mobile version