አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ270 ሚሊየን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ፡፡
ኢንተርፕራይዙ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 5 ሚሊየን 534 ሺህ 699 የትራፊክ ፍሰት በማስተናገድ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት እና ከልዩ ልዩ ገቢዎች 514 ሚሊየን 602 ሺህ 957 ብር ገቢ ማግኘት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
በዚህም ከታክስ በፊት 271 ሚሊየን 72 ሺህ 823 ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን÷ ከባለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 27 ነጥብ 8 በመቶ እድገት መመዝገቡን ከኢንተርፕራዙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢንተርፕራይዙ የትርፍ አፈፃፀምም ከዕቅዱ ጋር ሲነጻጸር 111 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል።