የሀገር ውስጥ ዜና

በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የተገነባው ህንጻ ለተጠቃሚዎች ተላለፈ

By Amele Demsew

February 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አነስተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የተገነባው ዘመናዊ ባለ አምስት ወለል ህንጻ ተመርቆ ለተጠቃሚዎች ተላልፏል።

ህንጻውን ጊፍት ሪል እስቴትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመተባበር ያስገነቡት ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣የጊፍት ሪል ስቴት ባለቤት ገብረየሱስ ኢጋታ እና የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አለምፀሀይ ሽፈራው በጋራ በመሆን ቤቶቹን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ ዛሬ የተላለፉትን 30 ቤቶችን ጨምሮ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ባለሃብቶችን በማስተባበር ከ5 ሺህ በላይ ቤቶች ተገንብተዋል፡፡

የልማት ጥውን ተቀብለው በዚህ የበጎ ስራ ለተሳተፉ ባለሃብቶችም ምስጋና አቅበዋል፡፡

ቤቶቹ የተሰጡት በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ11 ወረዳዎች ለተውጣጡ 30 አነስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

ቤቶቹ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆን÷ ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለ አንድ እና ባለሁለት መኝታ ቤቶችን ያካተቱ ናቸው።

በማህሌት ተ/ብርሃን