የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

February 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማርሾ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ የደጎል አደባባይን መልሶ ማልማት እንዲሁም በመዲናዋ ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎትን በጋራ መስራት ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡