Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቻይና-አፍሪካ ንግድ ልውውጥ 282 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ 282 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ለቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ቁልፍ መሰረት ነው፡፡

በፈረንጆቹ 2023 ቤጂንግ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የነበራት የንግድ ግንኙነትም ከምንጊዜውም በላይ ስኬታማ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

በበጀት ዓመቱም ቻይና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላት ዘርፈ ብዙ የንግድ ልውውጥ 282 ነጥብ 1 ቢሊየን በላይ መድረሱን ጠቁሟል፡፡

ይህም ቻይና ለ15 ተከታታይ ዓመታት ከአፍሪካ ጋር ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ያደረገች ብቸኛዋ ሀገር ያደርጋታል ተብሏል፡፡

በቀጣይ የቻይና-አፍሪካን የኢኮኖሚ እና ንግድ ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ አዲስ እቅድ ተነድፎ እየተሰራ እንደሆነ መገለጹንም ሺንዋ ዘግቧል፡፡

በዚህም የቻይናን ብሎም የአፍሪካ ሀገራትን ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version