የሀገር ውስጥ ዜና

ምርጫ ቦርድ ለ3 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ

By ዮሐንስ ደርበው

January 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ፡፡

ቦርዱ በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም በተሰጠው ሥልጣን መሠረት÷ ‘የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ ተብሎ ለሚጠራ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም ‘የኩሽ ሕዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ’ ተብሎ ለሚጠራ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ እና ‘ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ’ ለተባለ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን ቦርዱ አስታውቋል፡፡