አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ቻይና ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ሊያደርጉ መሆኑ ተመላከተ፡፡
የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበትን 75ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የቻይና መከላከያ ሚኒስትር ዶንግ ጁን ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ሾይጉ ጋር የቪዲዮ ውይይት አድርገዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በሁለቱም ሀገራት መሪዎች ስትራቴጂካዊ አመራር÷ ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቃል ገብተዋል።
የሀገራቱ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በአዲሱ ዘመን ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡን የጠቀሱት ዶንግ፤ የሀገራቱ መሪዎች መግባባት ለዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች በቆራጥነት ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ስልታዊ የጋራ መተማመንን በየጊዜው ማሳደግ፣ ተግባራዊ ትብብርን ማስፋት እና የሁለቱን ጦር ሃይሎች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እንዲችሉም ጠይቀዋል።
ዶንግ በተጨማሪም የሁለትዮሽ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ ቅንጅትን ለማጠናከር እና ዓለም አቀፍ ደህንነትን እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ የጋራ ጥረቶች እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
ሾይጉ በበኩላቸው÷ የሩስያ እና ቻይና ግንኙነት በታሪክ የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ሩሲያ የዘንድሮውን 75ኛ ዓመት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የምስረታ በዓል እንደ አዲስ መነሻ በመውሰድ በሁለቱ ጦር ኃይሎች መካከል ትብብርን ለመፍጠር እና የሁለቱን ሀገራት ወታደሮች ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከቻይና ጋር ለመስራት ዝግጁ ነች ብለዋል።
ሁለቱ ወገኖች በጋራ ጥቅም ላይ በሚውሉ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይም ሀሳብ መለዋወጣቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!