የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኡሞድ ለሕዝብ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አመራሩ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ አሳሰቡ

By ዮሐንስ ደርበው

January 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2106 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጋምቤላ ክልል ሕዝብ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት አመራሩ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ፡፡

የክልሉ መንግሥት የ2016 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ተገምግሟል።

ባለፉት ስድስት ወራት በአስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች በርካታ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡

በአንፃሩ የክልሉን ሕዝብ ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በርካታ ሥራዎችን ማከናወን የሚያስፈልግበት ወቅት ነው ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የክልሉን ሕዝብ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በሚደረገው ጥረትም አመራሩ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የድህነት ቅነሳ ላይ የሚሠሩ መሥሪያ ቤቶች የሥራ እንቅስቃሴም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላከልቷል፡፡