የሀገር ውስጥ ዜና

ጥንካሬዎቻችንን እያሳደግን፣ክፍተቶቻችንን እየሞላን በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Amele Demsew

January 30, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥንካሬዎቻችንን እያሳደግን፣ክፍተቶቻችንን እየሞላን ቃላችንን ጠብቀን በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ አመራሮች ጋር የከተማ አስተዳደሩን የስራ አፈፃፀም መገምገማቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የቀጣይ 90 ቀን የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብርም ማከናወናቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በህዝብ ተሳትፎ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል የስራ እድል ፈጠራ ፣የኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ፣የከተማ ግብርና እና የሌማት ትሩፋት ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋልም ነው ያሉት፡፡

ጥንካሬዎቻችንን እያላቅን ፣ክፍተቶቻችንን እየሞላን ቃላችንን ጠብቀን በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ሲሉም ገልጸዋል።