Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ተያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረጋችን አመሰግናቸዋለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ተጠናክረው የቀጠሉት ግንኙነቶቻችን በሁለቱ ሀገሮቻችን እያደገ ለመጣው ትብብር ዋቢ ናቸውም ብለዋል፡፡

Exit mobile version