Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማስመዝገቧ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለውጭ ያቀረበችው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን÷ በአጠቃላይ 238 ቢሊየን ዶላር መድረሱ ተገልጿል።
 
ለሽያጩ መጨመርም የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተጠቅሷል፡፡
 
የአሜሪካ መንግስት የ81 ቢሊየን ዶላር ሽያጭ ላይ በቀጥታ መደራደሩን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዘገበ ሲሆን÷ ይህም በ2022 ከነበረው የ56 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተመላክቷል።
 
የተቀረው የአሜሪካ መከላከያ ኩባንያዎች ለውጭ ሀገራት በቀጥታ ያደረጉት ሽያጭ እንደሆነ ነው የተነገረው።
 
ወታደራዊ ኃይሏን ለማስፋፋት ጥረት እያደረገች የምትገኘው ፖላንድ፤ አፓቼ ሄሊኮፕተሮችን ለመግዛት 12 ቢሊየን ዶላር፣ ለዘመናዊ ሮኬት ተኳሽ መሳሪያ 3 ነጥብ 75 ቢሊየን ዶላር፣ ለኤም1ኤ1 አብራምስ ታንኮች ደግሞ 10 ቢሊየን ዶላር መክፈሏን ሚኒስቴሩ በጥቅምት ወር ለተጠናቀቀው የአሜሪካ መንግስት የበጀት ዓመት ባወጣው ዘገባ አመልክቷል።
 
ለተቀናጀ የአየር እና የሚሳኤል መከላከያ የውጊያ ትዕዛዝ ስርዓትም 4 ቢሊየን ዶላር ማውጣቷ ተመላክቷል።
 
የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ ሀገራቸውን በአውሮፓ እጅግ ኃያል የምድር ኃይል ለማድረግ እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version