Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢሎን መስክ የመጀመሪያውን አንጎል ውስጥ የሚቀበር ቺፕ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቢሊየነሩ ኢሎን መስክ የኒውራሊንክ ኩባንያ ከገመድ አልባ ቺፖች መካከል አንዱን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው አንጎል ውስጥ በተሳካ ሁኔታ መቅበሩን አስታውቋል።
 
የመጀመሪያ ውጤቶችም ተስፋ ሰጪ እንደሆኑና ታካሚውም በጥሩ ሁኔታ እያገገመ እንደሚገኝ ተገልጿል።
 
ዓላማው የሰውን አእምሮ ከኮምፒዩተር ጋር ማገናኘት መሆኑን የገለጸው ኩባንያው ውስብስብ የነርቭ ህመሞችን ለመቅረፍ መርዳት እንደሚፈልግ ተናግሯል።
 
በርካታ ተቀናቃኝ ኩባንያዎችም ተመሳሳይ መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ ማዋላቸው ተመላክቷል።
 
የአሜሪካ የህክምና ቁጥጥር፣ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) የኢሎን መስክ ኩባንያ ከረጅም ትግል በኋላ ቺፕ በሰዎች ላይ ለመፈተሽ በፈረንጆቹ ግንቦት ወር 2023 ፍቃድ እንደተሰጠው ለቢቢሲ ገልጿል፡፡
 
ይህም ለስድስት ዓመታት የቆየው ጥናት ወደ ሥራ እንዲገባ የሚያስችል ተስፋ ሰጥቷል ሲልም አስተዳደሩ አክሏል።
 
እንደ ኒውራሊንክ ገለፃ አንድ ሮቦት እንቅስቃሴን በሚቆጣጠረው የአንጎል ክፍል ላይ ከሰው ፀጉር የቀጠኑ 64 ተጣጣፊ ክሮችን በቀዶ ጥገና ያስቀምጣል፡፡
 
እነዚህ ለሙከራ የተቀበሩ ክሮችም ያለገመድ ቻርጅ በሚደረግ ባትሪ የአንጎል ምልክቶችን ለመቅረጽ እና ሰውዬው እንዴት መንቀሳቀስ እንዳሰበ የሚፈታውን መተግበሪያ ለማስተላለፍ ያስችለዋል ሲል ኩባንያው አብራርቷል።
 
ኢሎን መስክ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክትም የኒውራሊንክ የመጀመሪያው ምርት ቴሌፓቲ ተብሎ እንደሚጠራ ገልፀዋል፡፡
 
ቴሌፓቲ አንድ ሰው ስልኩን ወይም ኮምፒዩተሩን እና በእነሱ አማካኝነት ማንኛውንም መሳሪያ በማሰብ ብቻ ለመቆጣጠር ያስችላል ብለዋል።
 
የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚዎችም አካል ጉዳተኞች (እጃቸውን) ያጡ ሰዎች እንደሚሆኑም አመላክተዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version