Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሐሰተኛ ሰነድ በማጭበርበር ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ተቀብሎ ተሰውሯል የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐሰተኛ ሰነድ አጭበርብሮ ከባለሃብት 13 ሚሊየን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ ተሰውሯል የተባለው ተጠርጣሪ ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንዳስታወቀው÷ ተጠርጣሪው በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሴንትራል ማተሚያ ቤት አካባቢ በሐሰተኛ ሠነድ በማጭበርበር 13 ሚሊየን 888 ሺህ ተቀብሎ ተሰውሯል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ክትትልም ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተጠርጣሪው ተታለልኩ ወይም ተጭበረበርኩ የሚል ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት ማድረግ ይችላል ተብሏል፡፡

ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር እንዳይታለል ራሱን እንዲጠብቅና በወንጀል መከላከል ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎም አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

Exit mobile version