Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያና በጀርመን መካከል እየተተገበሩ ባሉ የልማት ስራዎች ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል ስላለው በትምህርትና ሥልጠና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በድህነት ቅነሳ እየተተገበሩ ያሉ ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስታውቀዋል፡፡
 
በተጨማሪ በተያያዥ ጉዳዮች እና እየተተገበሩ ባሉ የልማትና የትብብር ሥራዎች ዙሪያ ከጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ፊሊፕ ኒል ጋር ውጤታማ ውይይት ማካሄዳቸውን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
 
በውይይታቸው÷ በሀገሪቱ የልማትና ትብብር ሥራ ውስጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሩ መግለፃቸውን ተናግረዋል፡፡
 
የጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ፊሊፕ ኒል ÷የሁለቱን ሀገራት የረዥም ጊዜ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነት ሚኒስትሯ አመስግነዋል፡፡
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version