የሀገር ውስጥ ዜና

የሉሲ ቅሬተ አካል የተገኘበት 50ኛ ዓመት እዮቤልዩ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል

By Shambel Mihret

January 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሉሲ ቅሬተ አካል የተገኘበት 50ኛ ዓመት እዮቤልዩ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት ለዓለም ማስተዋወቅ በሚያስችሉ ዝግጅቶች እንደሚከበር የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ÷የሉሲ ቅሬተ አካልን ካገኙት አርኪዎሎጂስት ዶናልድ ጆሃንሰን (ፕ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በሉሲ መገኛ 50ኛ ዓመት እዮቤልዩ መታሰቢያ የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት ለዓለም ማስተዋወቅ የሚያስችሉ መርሐ ግብሮችን ማዘጋጀት በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል፡፡

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) ሳተላይቱን በሉሲ ስም መሰየሙ ተጠቁሟል፡፡

ለዚህም ዶናልድ ጆሃንሰን(ፕ/ር) ላደረጉት አስተዋፅኦ አምባሳደር ናሲሴ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአርኪዮሎጂካል ቱሪዝምን ለማሳደግ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው እየተሰራ መሆኑንም የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡