Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተመድ ለጋዛ የሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለጋዛ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ሀገራት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

አሜሪካ ፣ ብሪታንያን፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፊንላንድ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ኔዘርላንድስ ለጋዛ ሲያደርጉት የነበረውን የሰብዓዊ እርዳታ ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሀገራቱ ድጋፉን ያቋረጡት ሃማስ በእስራኤል ላይ በፈጸመው ጥቃት በጋዛ እርዳታ የማስተባበርና የማሰራጭት ሥራ የሚሠራው የተመድ ኤጀንሲ ሰራተኞች መሳተፋቸውን እስራኤል ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ÷ በድርጊቱ ተሳትፋዋል የተባሉ ሠራተኞችን ከሥራ ማባረሩን እና ተጨማሪ ምርመራም ማካሄድ መጀመሩን በይፋ ገልጿል፡፡

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ÷አሁን ላይ በጋዛ የሚገኙ ከ2 ሚሊየን በላይ ዜጎች የዕለት ሰብዓዊ እርዳታ ጠባቂዎች ናቸው፡፡

በጋዛ የሰብዓዊ እርዳታ ሲያቀርቡ የነበሩ ሀገራት ድጋፋቸውን ማቋረጣቸውንም አስደንጋጭ ድርጊት ሲሉ ኮንነዋል፡፡

ስለሆነም ሀገራት በጋዛ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

የሃማስ ታጣቂዎች ባሳለፍነው መስከረም መጨረሻ በእስራኤል ላይ በፈጸሙት መብረቃዊ ጥቃት 1ሺህ 300 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷ 250 የሚሆኑት ደግሞ በእገታ መወሰዳቸው ይታወቃል፡፡

በአንጻሩ እስራኤል ጥቃቱን ተከትሎ በሃማስ ላይ እየወሰደች ባለው አጸፋዊ እርምጃ በጋዛ ከ26 ሺህ በላይ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ቲ አርቲ በዘገባው አስታውሷል፡፡

Exit mobile version