አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከክለቡ የ2023/24 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሐ-ግብር ሲጠናቀቅ ከክለቡ እንደሚሰናበቱ ተሰምቷል፡፡
የተጀመረው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር መርሐ-ግብር እስከሚጠነቀቅ ድረስ በአሰልጣኝነታቸው እንደሚቀጥሉም ተገልጿል፡፡
የመርሲሳይዱ ክልብ ሊቨርፑል አሁን ላይ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡
ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በፈረንጆቹ 2015 ሊቨርፑልን በዋና አሰልጣኝነት የተረከቡ ሲሆን በክለቡም ከ8 ዓመት ተኩል በላይ ቆይተዋል፡፡
በቆይታቸውም የፕሪሚየር ሊግ፣ የሻምፒዮንስ ሊግ፣ የኤፍ ኤ ካፕ፣ የካርሊን ካፕ፣ የዓለም የክለቦች ዋንጫን አንስተዋል፡፡
በዚህ ዓመት በቀጣይ ወር ለሚካሔደው የካርሊንግ ካፕ ዋንጫ ለፍፃሜ መድረሳቸውም ይታወቃል፡፡